የ ፊደል ገበታ በ መጠቀም ረድፍ ወይንም አምድ መጨመሪያ ወይንም ማጥፊያ ወደ ሰንጠረዥ ውስጥ
እርስዎ መጨመር ወይንም ማጥፋት ይችላሉ ረድፎች ወይንም አምዶች በ ሰንጠረዦች ውስጥ እንዲሁም መክፈል ወይንም ክፍሎች ማዋሀድ የ ፊደል ገበታ በ መጠቀም
-
አዲስ ረድፍ ለ መጨመር መጠቆሚያውን በ ሰንጠረዥ ክፍል ውስጥ ያድርጉ እና ይጫኑ ምርጫ Alt+ማስገቢያ: እና ከዛ ይጫኑ ቀስት ወደ ላይ ወይንም ወደ ታች ቁልፍ: እንዲሁም መጠቆሚያውን ወደ ሰንጠረዡ መጨረሻ ክፍል ያንቀሳቅሱ እና ከዛ ይጫኑ Tab.
-
አዲስ አምድ ለ መጨመር መጠቆሚያውን በ ሰንጠረዥ ክፍል ውስጥ ያድርጉ እና ይጫኑ ምርጫ Alt+ማስገቢያ: እና ከዛ ይጫኑ የ ግራ ወይንም የ ቀኝ ቀስት ቁልፎችን
-
የ ሰንጠረዥ ክፍል ለ መክፈል አምድ ከ መጨመር ይልቅ ይጫኑ ምርጫ Alt+ማስገቢያ: እና ከዛ ተጭነው ይያዙ ትእዛዝ Ctrl የ ግራ ወይንም የ ቀኝ ቀስት ቁልፎችን በሚጫኑ ጊዜ
-
ረድፍ ለ ማጥፋት መጠቆሚያውን በ ሰንጠረዥ ክፍል ውስጥ ያድርጉ እና ይጫኑ ምርጫ Alt+ማጥፊያ: እና ከዛ ይጫኑ ወደ ላይ ወይንም ወደ ታች የ ቀስት ቁልፎች
-
አምድ ለ ማጥፋት መጠቆሚያውን በ ሰንጠረዥ ክፍል ውስጥ ያድርጉ እና ይጫኑ ምርጫ Alt+ማጥፊያ እና ከዛ ይጫኑ የ ግራ ወይንም የ ቀኝ ቀስት ቁልፍ
-
ሰንጠረዥ ለ ማዋሀድ አጠገቡ ካለው ክፍል ጋር: መጠቆሚያውን ክፍሉ ውስጥ ያድርጉ እና ይጫኑ ምርጫ Alt+ማጥፊያ: ተጭነው ይያዙ ትእዛዝ Ctrl እና ከዛ ይጫኑ የ ግራ ወይንም የ ቀኝ ቀስት ቁልፍ